School
Tech
Home
About Us
Services
Pages
news
Note
Contact
Lang
English
|
አማርኛ
Admission
Login
Notes
Home
Pages
Notes
Make your School service Digital
Our Notes
የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከአምናው ጋር ተቀራራቢ ነው ተብሏል
በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና 649 ከፍተኛው ውጤት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ትምህርት ሚኒስቴር የ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት በ2015 ዓ.ም 845 ሺህ ተማሪዎች ፈተናው ላይ ተቀምጠው የማለፊያ ውጡ ወይም ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ ማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ብዛት 27 ሺህ 267 ብቻ ናቸው የተባለ ሲሆን 19 ሺህ 17 ከተፈጥሮ ሳይንስ 8ሺህ 250 ተማሪዎች ደግሞ ከማህበራዊ ሳይንስ ናቸው ተብሏል፡፡
649 የተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ሲመዘገብ በአዲስ አበባ ልደታ የሚገኝ ትምህርት ቤት ከፍተኛውን ውጤት ሲያስመዘገብ የማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 በአማራ ክልል ሐዲስ ዓለማየሁ ትምህርት ቤት መመዝገቡ ተገልጿል፡፡